ዘኍል 35:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሌዋውያንም የምትሰጡት የከተማ መሰማሪያ በከተማው ዙሪያ ሁሉ ከቅጥሩ ወደ ውጭ አንድ ሺህ ክንድ ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በየከተሞቹ ዙሪያ ለሌዋውያኑ የምትሰጧቸውም የግጦሽ መሬት ከከተማው ቅጥር አንድ ሺሕ ክንድ ይዘረጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግጦሽ መሬቱ ከከተማው ቅጽር ግንብ በሁሉ አቅጣጫ እስከ አራት መቶ ኀምሳ ሜትር ይስፋ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሌዋውያንም የምትሰጡት የከተማ መሰማርያ በከተማው ዙሪያ ከቅጥሩ ወደ ውጭ አንድ ሺህ ክንድ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሌዋውያንም የምትሰጡት የከተማ መሰምርያ በከተማው ዙሪያ ከቅጥሩ ወደ ውጭ አንድ ሺህ ክንድ ይሁን። |
ከከተማው ውጭ በምሥራቅ በኩል ሁለት ሺህ ክንድ፥ በደቡብ በኩል ሁለት ሺህ ክንድ፥ በምዕራብ በኩል ሁለት ሺህ ክንድ፥ በሰሜንም በኩል ሁለት ሺህ ክንድ ትለካላችሁ፥ ከተማውም በመካከል ይሆናል፤ ይህም የከተሞቹ መሰማሪያ ይሆንላቸዋል።