ዘኍል 35:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማኅበሩ በመቺውና በደም ተባቃዩ መካከል ፍርድን በዚህ መሠረት ይፍረድ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማኅበሩ በዚህ ሰውና በደመኛው መካከል በእነዚህ ደንቦች መሠረት ይፍረድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህ ያለው ሁኔታ በሚፈጸምበት ጊዜ ማኅበሩ በገዳዩና በተበቃዩ መካከል ፍርድ የሚሰጠው በሚከተለው ሥርዓት መሠረት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠላቱም ባይሆን፥ ክፉም ያደርግበት ዘንድ ባይሻ፥ ማኅበሩ በመቺውና በባለ ደሙ መካከል ፍርድን እንደዚህ ይፍረዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማኅበሩ በመቺውና በደም ተባቃዩ መካከል ፍርድን እንደዚሁ ይፍረድ፤ |
ማኅበሩም ነፍሰ ገዳዩን ከደም ተበቃዩ እጅ ያድነዋል፥ ማኅበሩም ወደ ሸሸበት ወደ መማፀኛ ከተማ ይመልሰዋል፤ በቅዱስ ቅባትም የተቀባው ታላቁ ካህን እስኪሞት ድረስ በዚያ ይቀመጣል።
በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ፥ በዚያም ወራት ያለው ታላቁ ካህን እስኪሞት ድረስ በዚያች ከተማ ይቀመጥ፤ ከዚያም ወዲያ ነፍሰ ገዳዩ ይመለሳል፥ ወደ ከተማውም ወደ ቤቱም ሸሽቶ ወደ ወጣበትም ከተማ ይገባል።’ ”