La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 32:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ ሄደው ምድሪቱን ባዩ ጊዜ፥ ጌታ ወደ ሰጣቸው ምድር እንዳይገቡ የእስራኤልን ልጆች ልብ አደከሙ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወደ ኤሽኮል ሸለቆ ሄደው ምድሪቱን ካዩ በኋላ፣ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው ምድር እንዳይገቡ እስራኤላውያንን ተስፋ አስቈረጧቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እስከ ኤሽኮል ሸለቆ ሄደው ምድሪቱን ተመለከቱ፤ ነገር ግን ከዚያ በተመለሱ ጊዜ ሕዝቡ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው ምድር እንዳይገቡ ተስፋ አስቈረጡ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ወይን ዘለላ ሸለቆ መጡ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አዩ​አት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ ሰጣ​ቸው ምድር እን​ዳ​ይ​ገቡ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ልብ መለሱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ በሄዱ ጊዜ፥ ምድሪቱንም ባዩ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው ምድር እንዳይገቡ የእስራኤልን ልጆች ልብ አደከሙ።

Ver Capítulo



ዘኍል 32:9
5 Referencias Cruzadas  

ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ መጡ፥ ከዚያም ከወይኑ አንድ ሙሉ ዘለላ የነበረበትን አረግ ቈረጡ፥ ከእነርሱም ሁለት ሰዎች በመሎጊያ ተሸከሙት፤ ደግሞም ከሮማኑ ከበለሱም አመጡ።


የእስራኤል ልጆች ከዚያ ስለ ቈረጡት ዘለላ የዚያን ስፍራ ስም የኤሽኮል ሸለቆ ብለው ጠሩት።


ተጉዘውም በፋራን ምድረ በዳ በቃዴስ ወዳሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ መጡ፤ ወሬውንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ ነገሩአቸው፥ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።