La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 32:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የምናሴም ልጅ ኢያዕር ሄዶ መንደሮቻቸውን ያዘ፥ እነርሱንም የኢያዕር መንደሮች ብሎ ጠራቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከምናሴ ነገድ የሆነው ኢያዕር መኖሪያቸውን ወስዶ፣ የኢያዕር መንደሮች ብሎ ሰየማቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከምናሴ ነገድ የሆነው ያኢር በአንዳንድ መንደሮች ላይ አደጋ ጥሎ ወሰዳቸው፤ “የያኢር መንደሮች” ብሎም ሰየማቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የም​ና​ሴም ልጅ ኢያ​ዕር ሄዶ መን​ደ​ሮ​ች​ዋን ወሰደ፤ የኢ​ያ​ዕ​ርም መን​ደ​ሮች ብሎ ጠራ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የምናሴም ልጅ ኢያዕር ሄዶ መንደሮችዋን ወሰደ፥ የኢያዕርም መንደሮች ብሎ ጠራቸው።

Ver Capítulo



ዘኍል 32:41
5 Referencias Cruzadas  

በገለዓድ ራሞት ቤን ጌቤር ተብላ የምትጠራው ከተማ፥ በገለዓድ የምናሴ ዘር የሆነው የያኢር ጐሣ ይዞታዎች የሆኑት መንደሮች፥ በባሳን አርጎብ ተብላ የምትጠራው ግዛት፥ እንዲሁም በሮቻቸው የነሐስ መወርወሪያ ባሉአቸው የቅጽር ግንቦች የተመሸጉ በድምሩ የስድሳ ታላላቅ መንደሮች አስተዳዳሪ።


የምናሴ ልጅ ያኢር፥ ባሳንን እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ ድረስ፥ የአርጎብን ግዛት ሁሉ ወሰደ፥ ይችንም የባሳን ምድር እስከ ዛሬ ድረስ በሚጠራበት የያኢር መንደሮች ብሎ ጠራ።


ግዛታቸውም ከመሃናይም ጀምሮ የባሳን ንጉሥ የዐግ መንግሥት፥ ባሳን ሁሉ፥ በባሳንም ያሉት የኢያዕር መንደሮች ሁሉ ስድሳው ከተሞች፥


ያኢር በሠላሳ አህዮች የሚጋልቡ ሠላሳ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ልጆቹም እስከ ዛሬ ድረስ የያኢር መንደሮች ተብለው የሚጠሩ ሠላሳ ከተሞች በገለዓድ ምድር ነበሯቸው።