ዘኍል 23:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ቃልን በበለዓም አፍ አድርጎ፦ “ወደ ባላቅ ተመለስ፥ እንዲህም ተናገር” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም በበለዓም አፍ መልእክት አስቀምጦ፣ “ወደ ባላቅ ተመልሰህ ይህን መልእክት ንገረው” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም በለዓም ለባላቅ መናገር የሚገባውን መልእክት ከሰጠው በኋላ ወደዚያ ተመልሶ እንዲሄድ ነገረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በበለዓም አፍ ቃልን አኖረ፤ “ወደ ባላቅ ተመለስ፤ እንዲህም በል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ቃልን በበለዓም አፍ አድርጎ፦ ወደ ባላቅ ተመለስ፥ እንዲህም በል አለው። |
ከእነርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በአንተ ላይ ያለው መንፈሴ በአፍህም ውስጥ ያደረግሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ ከአፍህ፥ ከዘርህም አፍ፥ ከዘር ዘርህም አፍ አይለይም፥ ይላል ጌታ።
እግዚአብሔርም ወደ በለዓም በሌሊት መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ሰዎቹ ሊጠሩህ መጥተው እንደሆነ፥ ተነሣ ከእነርሱም ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የምነግርህን ቃል ብቻ ታደርጋለህ።”
የጌታም መልአክ በለዓምን፦ “ከሰዎቹ ጋር ሂድ፥ ነገር ግን የምነግርህን ቃል ብቻ ትናገራለህ” አለው። በለዓምም ከባላቅ ሹማምንት ጋር ሄደ።
እግዚአብሔርም ወደ በለዓም መጣ፤ እርሱም፦ “ሰባት መሠዊያዎች አዘጋጀሁ፥ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈንና አንድ አውራ በግ አሳረግሁ” አለው።