ዘኍል 23:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባላቅም በለዓምን እንዲህ አለው፦ “እባክህ ና፥ ወደ ሌላ ስፍራ እወስድሃለሁ፤ ምናልባት በዚህ ሆነህ እነርሱን ብትረግምልኝ እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝ ይሆናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ባላቅ በለዓምን፣ “በል እንግዲያው ወደ ሌላ ቦታ ልውሰድህ፤ ከዚያ ሆነህ እንድትረግምልኝ ምናልባት እግዚአብሔር ይፈቅድልህ ይሆናል” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባላቅም “ና ወደ ሌላ ቦታ እንሂድ፤ ምናልባት ከዚያ ሆነህ ይህን ሕዝብ እንድትረግምልኝ እግዚአብሔር ይፈቅድልህ ይሆናል” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባላቅም በለዓምን አለው፥ “ና፥ ወደ ሌላ ስፍራ እወስድሃለሁ፤ ምናልባት በዚህ ሆነህ እነርሱን ትረግምልኝ ዘንድ እግዚአብሔር ይወድድ ይሆናል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባላቅም በለዓምን፦ ና፥ ወደ ሌላ ስፍራ እወስድሃለሁ፤ ምናልባት በዚህ ሆነህ እነርሱን ትረግምልኝ ዘንድ እግዚአብሔር ይወድዳል አለው። |
አሁንም ከእኔ ይልቅ እጅግ ኃያል ናቸውና ልወጋቸውና ከምድሪቱ ላሳድዳቸው እችል እንደሆነ፥ ይህን ሕዝብ እባክህ፥ ና ርገምልኝ፤ አንተ የባረከው ቡሩክ የረገምኸውም ርጉም እንደሆነ አውቃለሁና።”
ባላቅም እንዲህ አለው፦ “በዚያ ሆነህ እንድታያቸው፥ እባክህ፥ ከእኔ ጋር ወደ ሌላ ቦታ ና፤ ዳርቻቸውንም ብቻ ታያለህ፥ ሁሉን ግን አታይም፤ በዚያም ሆነህ እነርሱን ርገምልኝ።”