La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 23:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ እርሱም መጣ፥ እነሆም፥ እርሱ ከእርሱም ጋር የሞዓብ ሹማምንቶች በሚቃጠለው መሥዋዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ ባላቅም፦ “ጌታ የተናገረው ምንድነው?” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱም ተመልሶ ሲሄድ ባላቅን ከመላው የሞዓብ አለቆች ጋራ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አገኘው፤ ባላቅም፣ “እግዚአብሔር ምን አለ?” ሲል ጠየቀው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርሱም ተመልሶ ሲሄድ ባላቅ ከሞአብ መሪዎች ጋር በዚያው በሚቃጠለው መሥዋዕት አጠገብ እንደ ቆመ አገኘው፤ ባላቅም እግዚአብሔር ምን እንደ ነገረው ጠየቀው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ እር​ሱም መጣ፤ እነሆ፥ እርሱ ከእ​ር​ሱም ጋር የሞ​ዓብ አለ​ቆች በመ​ሥ​ዋ​ዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ ባላ​ቅም በለ​ዓ​ምን አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምን አለ?”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ እርሱም መጣ፥ እነሆም፥ እርሱ ከእርሱም ጋር የሞዓብ አለቆች በመሥዋዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ ባላቅም፦ እግዚአብሔር የተናገረው ምንድር ነው? አለው።

Ver Capítulo



ዘኍል 23:17
5 Referencias Cruzadas  

ንጉሡ ሴዴቅያስ ልኮ አስመጣው፥ ንጉሡም በቤቱ፦ “በውኑ ከጌታ ዘንድ የሆነ ቃል አለን?” ብሎ በድብቅ ጠየቀው። ኤርምያስም፦ “አዎን አለ” ብሎ መለሰ። ከዚያም በኋላ፦ “በባቢሎን ንጉሥ እጅ ተላልፈህ ትሰጣለህ” አለ።


ጌታም በለዓምን አገኘው፥ ቃልንም በአፉ አድርጎ፦ “ወደ ባላቅ ተመለስ፥ እንዲህም ተናገር” አለው።


በለዓምም ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “ባላቅ ሆይ! ተነሣ፥ ስማም፤ የሴፎር ልጅ ሆይ! አድምጠኝ፤


በለዓምም መልሶ ባላቅን፦ “ ‘ጌታ የተናገረውን ሁሉ አደርጋለሁ’ ብዬ ነግሬህ አልነበረምን?” አለው።


ዔሊም፥ “እርሱ የነገረህ ነገር ምንድነው? አትደብቀኝ፤ ከነገረህ ውስጥ አንዲቱን እንኳ ብትደብቀኝ እግዚአብሔር እንደዚያው ያድርግብህ፤ ከዚያ የከፋም ያምጣብህ” አለው።