ዘኍል 23:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም17 እርሱም ተመልሶ ሲሄድ ባላቅን ከመላው የሞዓብ አለቆች ጋራ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አገኘው፤ ባላቅም፣ “እግዚአብሔር ምን አለ?” ሲል ጠየቀው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ወደ እርሱም መጣ፥ እነሆም፥ እርሱ ከእርሱም ጋር የሞዓብ ሹማምንቶች በሚቃጠለው መሥዋዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ ባላቅም፦ “ጌታ የተናገረው ምንድነው?” አለው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 እርሱም ተመልሶ ሲሄድ ባላቅ ከሞአብ መሪዎች ጋር በዚያው በሚቃጠለው መሥዋዕት አጠገብ እንደ ቆመ አገኘው፤ ባላቅም እግዚአብሔር ምን እንደ ነገረው ጠየቀው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ወደ እርሱም መጣ፤ እነሆ፥ እርሱ ከእርሱም ጋር የሞዓብ አለቆች በመሥዋዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ ባላቅም በለዓምን አለው፥ “እግዚአብሔር ምን አለ?” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ወደ እርሱም መጣ፥ እነሆም፥ እርሱ ከእርሱም ጋር የሞዓብ አለቆች በመሥዋዕቱ ዘንድ ቆመው ነበር፤ ባላቅም፦ እግዚአብሔር የተናገረው ምንድር ነው? አለው። Ver Capítulo |