ዘኍል 22:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አህያይቱም የጌታን መልአክ አይታ ወደ ቅጥሩ ተጠጋች፥ የበለዓምንም እግር ከቅጥሩ ጋር አጣበቀች፤ እርሱም ዳግመኛ መታት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አህያዪቱም የእግዚአብሔርን መልአክ ባየች ጊዜ ወደ ግንቡ ተጠግታ የበለዓምን እግር አጣበቀችው፤ ስለዚህም እንደ ገና መታት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አህያይቱ መልአኩን ባየች ጊዜ ወደ ግንቡ ተጠግታ የበለዓምን እግር ከግንቡ ጋር አጣበቀችው፤ በለዓም አሁንም አህያይቱን መደብደብ ጀመረ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አህያዪቱም የእግዚአብሔርን መልአክ አይታ ወደ ቅጥሩ ተጠጋች፤ የበለዓምንም እግሩን ላጠችው፤ እርሱም ደግሞ መታት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አህያይቱም የእግዚአብሔርን መልአክ አይታ ወደ ቅጥሩ ተጠጋች፥ የበለዓምንም እግር ከቅጥሩ ጋር አጣበቀች፤ እርሱም ደግሞ መታት። |