La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 18:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ለሌዋውያን ተናገር እነርሱንም እንዲህ በላቸው፦ ‘ከእስራኤል ልጆች ለእናንተ ርስት አድርጌ የሰጠኋችሁን አሥራት በተቀበላችሁ ጊዜ፥ ከእርሱ ለጌታ ለስጦታ የሚቀርበውን ቁርባን የአሥራት አሥራት ታቀርባላችሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ሌዋውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ርስት አድርጌ የምሰጣችሁን ዐሥራት ከእስራኤላውያን በምትቀበሉበት ጊዜ፣ እናንተም ካገኛችሁት ላይ አንድ ዐሥረኛ በማውጣት ለእግዚአብሔር መባ አድጋችሁ ታቀርባላችሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ለሌዋውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘እግዚአብሔር ድርሻችሁ አድርጎ የሚሰጣችሁን ዐሥራት ከእስራኤላውያን በምትቀበሉበት ጊዜ፥ እናንተም በበኩላችሁ ከዚያው ከተቀበላችሁት የዐሥራት ዐሥራት በማውጣት ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጋችሁ አቅርቡ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ለሌ​ዋ​ው​ያን እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከእ​ና​ንተ ርስት አድ​ርጌ የሰ​ጠ​ኋ​ች​ሁን ዐሥ​ራት በተ​ቀ​በ​ላ​ችሁ ጊዜ፥ እና​ን​ተ​ም​ከ​እ​ርሱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አድ​ር​ጋ​ችሁ የዐ​ሥ​ራት ዐሥ​ራት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለሌዋውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ከእስራኤል ልጆች ለእናንተ ርስት አድርጌ የሰጠኋችሁን አሥራት በተቀበላችሁ ጊዜ፥ ለእግዚአብሔር ለማንሣት ቍርባን የአሥራት አሥራት ታቀርባላችሁ።

Ver Capítulo



ዘኍል 18:26
7 Referencias Cruzadas  

ሌዋውያኑም አሥራቱን በተቀበሉ ጊዜ የአሮን ልጅ ካህኑ ከሌዋውያን ጋር ይሁን፥ ሌዋውያኑም የአሥራቱን አሥራት ወደ አምላካችን ቤት ወደ ጓዳዎች ወደ ዕቃ ቤት ያምጡት።


የእስራኤል ልጆችና የሌዊ ልጆችም የእህሉንና የወይኑን የዘይቱንም የማንሣት ቁርባንን የመቅደሱ ዕቃዎችና የሚያገለግሉት ካህናት በረኞቹና መዘምራኑ ወዳሉባቸው ጓዳዎች ያግቡት፥ እንዲሁም የአምላካችንን ቤት ከቶ አንተውም።


መጀመሪያ ከምታዘጋጁት ሊጥ እንደ ስጦታ አድርጋችሁ የምታቀርቡትን ቁርባን እስከ ልጅ ልጃችሁ ለጌታ ትሰጣላችሁ።


ለሌዊም ልጆች፥ እነሆ፥ በመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ስለሚያገለግሉ፥ የእስራኤልን ልጆች አሥራት ሁሉ ርስት አድርጌ ሰጥቼአለሁ።


ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


እንደ ስጦታ የምታቀርቡት ቁርባናችሁም እንደ አውድማው እህልና እንደ ወይን መጭመቂያው ሙላት ይቈጠርላችኋል።


ከሌዊ ልጆችም፥ ክህነትን የሚቀበሉት ከሕዝቡ ማለት ከወንድሞቻቸው፥ እነዚያ ክህነትን የሚቀበሉት የሌዊ ልጆች ከሕዝቡ ማለትም ከወንድሞቻቸው፥ እነርሱ ምንም ከአብርሃም ወገብ ቢወጡ፥ አሥራትን እንዲቀበሉ በሕግ ታዞላቸዋል።