La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 15:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለአንዱም አውራ በግ የኢን መስፈሪያ ሢሶ በሆነ ዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ የሆነ መልካም ዱቄት ለእህል ቁርባን እንዲሆን ታዘጋጃለህ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘ከአውራ በግ ጋራ በሂን ሢሶ ዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ ልም ዱቄት የእህል ቍርባን አዘጋጁ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አውራ በግ መሥዋዕት ሆኖ በሚቀርብበት ጊዜ ደግሞ በአንድ ሊትር ተኩል የወይራ ዘይት የተለወሰ ሁለት ኪሎ ዱቄት አቅርቡ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለአ​ን​ዱም አውራ በግ የሚ​ቃ​ጠል ቍር​ባን ወይም መሥ​ዋ​ዕት ባደ​ረ​ጋ​ችሁ ጊዜ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ሢሶ በሆነ ዘይት የተ​ለ​ወሰ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያው ከዐ​ሥር እጅ ሁለት እጅ መል​ካም ዱቄት ለእ​ህል ቍር​ባን ታዘ​ጋ​ጃ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለአንዱም አውራ በግ ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን የኢን መስፈሪያ ሢሶ በሆነ ዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከአሥር እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት ለእህል ቍርባን ታዘጋጃለህ፤ የኢን መስፈሪያ ሢሶም የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቍርባን ታቀርባለህ።

Ver Capítulo



ዘኍል 15:6
5 Referencias Cruzadas  

“ቁርባኑም ፍየል ቢሆን በጌታ ፊት ያቀርበዋል፤


ቁርባኑን ለማቅረብ የሚያመጣ ሰው የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ አንድ እጅ የሆነ መልካም ዱቄትን የእህል ቁርባን አድርጎ ለጌታ ያቅርብ፤


የኢንም መስፈሪያ አራተኛ እጅ የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቁርባን ከሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ከሌላ መሥዋዕት ጋር ለእያንዳንዱ ጠቦት ታዘጋጃለህ።


ለጌታም መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን የኢን መስፈሪያ ሢሶ የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቁርባን ታቀርባለህ።