ሰዎች ከሩቅ የሚመጡት ስለ ታላቁ ስምህ፥ ስለ ጠንካራዪቱ እጅህ፥ ስለ ተዘረጋችው ክንድህ ሰምተው ነውና፤ እንግዳው መጥቶ ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቢጸልይ፥
ዘኍል 15:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጻተኛም ከእናንተ ጋር ቢቀመጥ፥ ወይም በትውልዳችሁ መካከል ማንም ሰው ቢኖር፥ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ቢያቀርብ፥ እናንተ እንደምታደርጉት እርሱ እንዲሁ ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ መጻተኛ ወይም በመካከላችሁ የሚኖር ማንኛውም ሰው በእሳት የሚቀርብ ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ ልክ እናንተ እንደምታደርጉት ያድርግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእናንተ ጋር ያለ ወይም በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛ መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የምግብ ቊርባን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ቢፈልግ፥ ይህንኑ የሥርዓት መመሪያ በተመሳሳይ ሁኔታ መከተል ይኖርበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጻተኛም ከእናንተ ጋር ቢቀመጥ፥ ወይም በትውልዳችሁ መካከል ማንም ሰው ቢኖር፥ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን ቍርባን በእሳት ቢያቀርብ እናንተ የምታደርጉትን እርሱ እንዲሁ ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጻተኛም ከእናንተ ጋር ቢቀመጥ፥ ወይም በትውልዳችሁ መካከል ማንም ሰው ቢኖር፥ ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን ቍርባን በእሳት ቢያቀርብ፥ እናንተ የምታደርጉትን እርሱ እንዲሁ ያደርጋል። |
ሰዎች ከሩቅ የሚመጡት ስለ ታላቁ ስምህ፥ ስለ ጠንካራዪቱ እጅህ፥ ስለ ተዘረጋችው ክንድህ ሰምተው ነውና፤ እንግዳው መጥቶ ወደዚህ ቤተ መቅደስ ቢጸልይ፥
“ለአሮንና ለልጆቹ ለእስራኤልም ልጆች ሁሉ እንዲህ ብለህ ለእነርሱ ተናገር፦ ከእስራኤል ቤት ወይም ከእናንተ መካከል ከሚቀመጥ እንግዳ ማናቸውም ሰው ስእለቱን ሁሉ፥ ለጌታም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ በፈቃዱ የሚያቀርበውን ቁርባን ሁሉ ቢያቀርብ፥
ከእንግዳም ሰው እጅ የተገኙ እንደነዚህ ያሉ እንስሶችን ሁሉ ለአምላካችሁ እንጀራ እንዲሆኑ አታቅርቡ፤ ርኩሰትም ነውርም አለባቸውና አይሠምሩላችሁም።”
የአገሩ ተወላጅ የሆነ ሁሉ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ባቀረበ ጊዜ እነዚህን ነገሮች እንዲሁ ያደርጋል።
ለእናንተና በእናንተ መካከል ለሚቀመጥ መጻተኛ ለጉባኤው ሁሉ አንድ ዓይነት ሥርዓት ይኑር፥ ለልጅ ልጃችሁም የዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል፤ እናንተ እንደ ሆናችሁት መጻተኛውም በጌታ ፊት እንዲሁ ይሆናል።