La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 11:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነፋስም ከጌታ ዘንድ ወጣ፥ ከባሕርም ድርጭቶችን አመጣ፥ እነርሱንም የአንድ ቀን መንገድ ያህል በዚህ፥ የአንድ ቀንም መንገድ ያህል በዚያ በሰፈሩ አጠገብ በተናቸው፤ በዚያም በሰፈሩ ዙሪያ ከፍታው ከምድር ወደ ላይ ሁለት ክንድ ያህል ቈለላቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ ነፋስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጥቶ ድርጭቶችን ከባሕር ወደ ሰፈር አመጣ፤ በየአቅጣጫውም ከፍታው ሁለት ክንድ፣ ርቀቱም የአንድ ቀን መንገድ ያህል እስኪሆን ድረስ በሰፈሩ ዙሪያ ከመራቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በድንገትም እግዚአብሔር ድርጭቶችን ከባሕር እየነዳ የሚያመጣ ነፋስ ላከ፤ ድርጭቶችም ከምድር አንድ ሜትር ያኽል ከፍ ብለው እየበረሩ መጡ፤ በሰፈሩና በሰፈሩ ዙሪያ የተከማቹበት ስፍራ የአንድ ቀን መንገድ ያኽል ነው፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነፋ​ስም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጣ፤ ከባ​ሕ​ርም ድር​ጭ​ቶ​ችን አወጣ፤ የአ​ንድ ቀንም መን​ገድ ያህል በዚህ፥ የአ​ንድ ቀንም መን​ገድ ያህል በዚያ በሰ​ፈሩ ላይ በተ​ና​ቸው፤ በዚ​ያም በሰ​ፈሩ ዙሪያ ከፍ​ታው ከም​ድር ወደ ላይ ሁለት ክንድ ነበረ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነፋስም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጣ፥ ከባሕርም ድርጭቶችን አመጣ፥ የአንድ ቀንም መንገድ ያህል በዚህ፥ የአንድ ቀንም መንገድ ያህል በዚያ በሰፈሩ ላይ በተናቸው፤ በዚያም በሰፈሩ ዙሪያ ከፍታው ከምድር ወደ ላይ ሁለት ክንድ ነበረ።

Ver Capítulo



ዘኍል 11:31
9 Referencias Cruzadas  

ለመኑ፥ ድርጭትንም አመጣላቸው፥ የሰማይንም እንጀራ አጠገባቸው።


የለመኑትንም ሰጣቸው፥ ለነፍሳቸው ግን ክሳትን ላከ።


ከምድር ዳርቻ ደመናትን ያወጣል፥ በዝናብ ጊዜ መብረቅን ያደርጋል፥ ነፋሳትንም ከመዛግብቱ ያወጣል።


ሙሴም በግብጽ ምድር ላይ በትሩን ዘረጋ፥ ጌታም የምሥራቅን ነፋስ ያን ቀን ሁሉ ሌሊቱን ሁሉ አመጣ፤ በነጋም ጊዜ የምሥራቁ ነፋስ አንበጣዎቹን አመጣ።


ጌታም ከምዕራብ ዐውሎ ነፋሱን መለሰ፥ አንበጣዎቹንም ወስዶ በኤርትራ ባሕር ውስጥ ጣላቸው፤ አንድ ስንኳ አንበጣ በግብጽ አገር አልቀረም።


ትንፋሽህን እፍ አልክባቸው፥ ባሕርም ከደናቸው፤ በኃይለኞች ውኆችም እንደ ብረት ሰጠሙ።


እንዲህም ሆነ በመሸ ጊዜ ድርጭቶች መጡ፥ ሰፈሩንም ሸፈኑት ማለዳም በሰፈሩ ዙሪያ ጤዛ ነበር።


ሙሴም ከእስራኤል ሽማግሌዎች ጋር ወደ ሰፈር ተመለሰ።