ዘኍል 10:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሁለተኛውም ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በሀያኛው ቀን እንዲህ ሆነ፤ ደመናው ከምስክሩ ማደሪያ ላይ ተነሣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሁለተኛው ዓመት፣ ሁለተኛው ወር በገባ በሃያኛው ቀን ደመናው ከምስክሩ ማደሪያ ላይ ተነሣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡ ከግብጽ ምድር በወጡ በሁለተኛው ዓመት፥ ሁለተኛው ወር በገባ በሃያኛው ቀን ከምስክሩ ድንኳን በላይ የረበበው ደመና ተነሣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሁለተኛውም ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያኛው ቀን እንዲህ ሆነ፤ ደመናው ከምስክሩ ድንኳን ላይ ተነሣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሁለተኛውም ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በሀያኛው ቀን እንዲህ ሆነ፤ ደመናው ከምስክሩ ማደሪያ ላይ ተነሣ። |
ጌታም ሙሴን በሲና ምድረ በዳ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፥ በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን፥ ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ዓመት እንዲህ ብሎ ተናገረው፦
በመጀመሪያውም ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በሲና ምድረ በዳ የፋሲካን በዓል አከበሩ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉ።