ነህምያ 9:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አርባ ዓመትም በምድረ በዳ መገብካቸው፤ ምንም አላጡም፤ ልብሳቸው አላረጀም፥ እግራቸውም አላበጠም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድረ በዳ አርባ ዓመት መገብሃቸው፤ ምንም ያጡት አልነበረም፤ ልብሳቸው አላለቀም፤ እግራቸውም አላበጠም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አርባ ዓመት ሙሉ በበረሓ ረዳሃቸው፤ ከሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ምንም አላሳጣሃቸውም፤ ልብሳቸው አላለቀም፤ እግራቸው አላበጠም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አርባ ዓመትም በምድረ በዳ መገብሃቸው፤ ምንም አላሳጣሃቸውም፤ ልብሳቸውም አላረጀም፤ እግራቸውም አላበጠም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አርባ ዓመትም በምድረ በዳ መገብሃቸው፥ ምንም አላጡም፥ ልብሳቸውም አላረጀም፥ እግራቸውም አላበጠም። |
“ጌታ አምላክህ የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና፥ በዚህ በታላቅ ምድረ በዳ መሄድህን አውቆአል፥ በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ ጌታ አምላክህ ከአንተ ጋር ነበረ፥ አንዳችም አላጣህም።
ጌታ አምላክህ ሊያስጨንቅህ፥ ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደሆነ፥ በልብህ ያለውን ያውቅ ዘንድ ሊፈትንህ፥ በእነዚህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ የመራህን መንገድ ሁሉ አስታውስ።