በብድር የያዛችሁትን እርሻቸውን፥ የወይን ቦታቸውን፥ ወይራቸውን፥ ቤታቸውን፥ ከመቶ አንድ የወሰዳችሁትን ብር፥ እህሉን፥ አዲሱን ወይን ጠጅና ዘይት እባካችሁ ዛሬ መልሱላቸው።”
ነህምያ 5:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህ የሚሉም ነበሩ፦ “በራቡ ጊዜ እህል እንድንወስድ እርሻችን፥ የወይን ቦታችንንና ቤታችንን አስይዘናል” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌሎቹ፣ “በራቡ ወቅት እህል ለማግኘት ስንል ዕርሻችንን፣ የወይን ተክል ቦታችንንና ቤታችንን እስከ ማስያዝ ደርሰናል” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሎቹ ደግሞ “ከደረሰብን ብርቱ ራብ ሕይወታችንን ለማትረፍ የሚያስችል እህል ለማግኘት ስንል እርሻችንን፥ የወይን ተክላችንንና ቤታችንን ሁሉ መያዣ አድርገን እስከ መስጠት ደርሰናል” ይሉ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከራብ የተነሣም እህልን እንሸምት ዘንድ እርሻችንንና ወይናችንን፥ ቤታችንንም አስይዘናል” የሚሉ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አያሌዎቹም፦ ከራብ የተነሣ እህልን እንሸምት ዘንድ እርሻችንና ወይናችንን ቤታችንንም አስይዘናል ይሉ ነበር። |
በብድር የያዛችሁትን እርሻቸውን፥ የወይን ቦታቸውን፥ ወይራቸውን፥ ቤታቸውን፥ ከመቶ አንድ የወሰዳችሁትን ብር፥ እህሉን፥ አዲሱን ወይን ጠጅና ዘይት እባካችሁ ዛሬ መልሱላቸው።”
“አምላክህ ጌታ በሚሰጥህ ምድር ላይ ካሉት ከተሞች በአንዲቱ ውስጥ ድኻ ቢኖር፥ በድኻ ወንድምህ ላይ ልብህን አትጨክንበት፤ ወይም እጅህን አትሰብስብበት።