ሚክያስ 5:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማይታዘዙ አሕዛብ ላይ በቁጣና በመዓት እበቀላለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአሼራ ምስልን ዐምድ ከመካከላችሁ እነቅላለሁ፤ ከተሞቻችሁንም እደመስሳለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአሼራን ምስል ከምድራችሁ እነቃቅላለሁ፤ ከተሞቻችሁንም አፈራርሳለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የማምለኪያ ዐፀዶችህንም ከመካከልህ እነቅላለሁ፥ ከተሞችህንም አፈርሳለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማምለኪያ ዐፀዶችህንም ከመካከልህ እነቅላለሁ፥ ከተሞችህንም አፈርሳለሁ። |
ስለዚህም የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ፥ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፥ ይህም ኃጢአትን የማስወገድ ፍሬ ነው።
ቤት። ጌታ የያዕቆብን ማደሪያዎች ሁሉ ዋጠ፥ አልራራምም፥ በመዓቱ የይሁዳን ሴት ልጅ አምቦች አፈረሰ፥ ወደ ምድርም አወረዳቸው መንግሥቱንና አለቆችዋን አረከሰ።
ጌታ ከእንግዲህ ወዲህ በስምህ እንዳይዘራ ስለ አንተ አዝዞአል፤ ከአምላኮችህ ቤት ጣዖትንና ቀልጦ የተሠራውን ምስል አጠፋለሁ። አንተም የማትረባ ነህና መቃብርህን እምሳለሁ።