ሚክያስ 2:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የያዕቆብ ቤት ሆይ፥ ይህ መባል አለበትን? በውኑ የጌታ መንፈስ ይቆጣልን? ሥራዎቹስ እነዚህ ናቸውን? ቃሎቼስ በቅን ለሚሄድ መልካም ነገር አያደርጉምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ እንዲህ ሊባል ይገባልን? “የእግዚአብሔር መንፈስ የማይታገሥ ነውን? እንዲህ ያሉ ነገሮችንስ ያደርጋልን?” “መንገዱ ቀና ለሆነ፣ ቃሌ መልካም አያደርግምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንግግራቸውንም በመቀጠል! “የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ ይህ መባል አለበትን? የእግዚአብሔር ትዕግሥት አልቋልን? እነዚህስ የእርሱ ድርጊቶች ናቸውን?” ብለው ይጠይቃሉ፤ ለመሆኑ አካሄዳቸው ቀጥተኛ ለሆነ የእኔ ቃላት መልካም ነገር አያደርጉምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የያዕቆብ ቤት የተባልህ ሆይ፥ በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ የማይታገሥ ነውን? ወይስ ሥራው እንደዚያች ናትን? ቃሌስ በቅን ለሚሄድ በጎነት አያደርግምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የያዕቆብ ቤት የተባልህ ሆይ፥ በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ የማይታገሥ ነውን? ወይስ ሥራው እንደዚያች ናትን? ቃሌስ በቅን ለሚሄድ በጎነት አያደርግምን? |
ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፥ በክፉዎች ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት ደጃፍ ላይ መቅረትን መረጥሁ።
በመጣሁስ ጊዜ ሰው ስለምን አልነበረም? በጠራሁስ ጊዜ የሚመልስ ስለምን አልነበረም? መታደግ እንዳትችል እጄ አጭር ሆናለችን? ወይስ ለማዳን ኃይል የለኝም? እነሆ፥ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፥ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም አጥተው ዓሦቻቸው ይገማሉ፥ በጥማትም ይሞታሉ።
ኤፍሬም ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ ከጣዖታት ጋር እኔ ምን አደርጋለሁ? እኔ እመልስለታለሁ፥ ወደ እርሱም እመለከታለሁ፤ እኔ እንደ ለመለመ ጥድ ነኝ፤ ፍሬህ በእኔ ዘንድ ይገኛል።
ፍትሕን የምትጠሉ፥ ትክክለኛውንም ነገር ሁሉ የምታጣምሙ እናንተ የያዕቆብ ቤት አለቆችና የእስራኤል ቤት ገዢዎች ሆይ፥ እባካችሁ ይህን ስሙ፦
እንግዲህ መልካም የሆነው ነገር ሞት ሆነብኝን? በጭራሽ! ነገር ግን ኃጢአት ኃጢአትነቱ እንዲታይ፥ መልካም በሆነው ነገር ሞትን ይሠራብኝ ነበር። ይኸውም ኃጢአት በትእዛዝ አማካይነት ያለ ልክ ኃጢአት እንዲሆን ነው።