La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 6:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ስትጸልዩ እንደ አሕዛብ የሚደጋገሙ ቃላትን አትጠቀሙ፥ እነርሱ ብዙ በመናገራቸው የሚሰሙ ይመስላቸዋልና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስትጸልዩ፣ ከንቱ ቃላት በመደጋገም ጸሎታቸው የሚሰማላቸው እንደሚመስላቸው አሕዛብ ነገራችሁን አታስረዝሙ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“እናንተ ስትጸልዩ እንደ አሕዛብ ከንቱ ቃል በመደጋገም አትለፍልፉ፤ እነርሱ በመደጋገማቸው ብዛት እግዚአብሔር ጸሎታቸውን የሚሰማቸው ይመስላቸዋል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 6:7
11 Referencias Cruzadas  

ከፍ ካለው ባለ ሥልጣን በላይ ሌላ ከፍ ያለ ይመለከታልና፥ ከእነርሱም በላይ ደግሞ ሌሎች ከፍ ይላሉና በአገሩ ድሆች ሲገፉ፥ ፍርድና ጽድቅም ሲነጠቅ ባየህ ጊዜ በዚህ ነገር አትደነቅ።


እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ቤተ ክርስቲያንንም ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ቁጠረው።


ወደ ፊት ጥቂት እልፍ ብሎ በፊቱ ተደፋና እንዲህ ሲል ጸለየ “አባቴ! የሚቻል ከሆነ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን እንደ አንተ ፈቃድ እንጂ እንደ እኔ አይሁን።”


እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ ሄዶ “አባቴ ሆይ! ይህንን ሳልጠጣው ሊያልፍ የማይቻል ከሆነ፥ ፈቃድህ ይሁን” ብሎ ጸለየ።


እንደገና ትቶአቸው ሄደ፤ ያንኑ ቃል ለሦስተኛ ጊዜ ደግሞ ጸለየ።


አሕዛብም እነዚህን ሁሉ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃል።


አይሁዳዊ ግን እንደሆነ ባወቁ ጊዜ፥ ሁሉ በአንድ ድምፅ “የኤፌሶን አርጤምስ ታላቅ ናት!” እያሉ ሁለት ሰዓት ያህል ጮኹ።