ማቴዎስ 5:48 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተም ፍጹሞች ሁኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ። |
እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝና፤ ስለዚህ ራሳችሁን ቀድሱ፥ ቅዱሳንም ሁኑ፥ እኔ ቅዱስ ነኝና፤ በምድርም ላይ በደረታቸው እየተሳቡ በሚርመሰመሱ ሁሉ የገዛ አካላችሁን አታርክሱ።
ይህን በማድረግ በሰማያት ላለው አባታችሁ ልጆች እንድትሆኑ ነው፤ እርሱ ለክፉዎችና ለደጎች ፀሐዩን ያወጣልና፥ ለጻድቃንና ለኃጥኣንም ዝናቡን ያዘንባልና።
በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! ደኅና ሁኑ። ፍጹማን ሁኑ፤ ምክሬን ስሙ፤ በአንድ ልብ ሁኑ፤ በሰላም ኑሩ፤ የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
እንግዲህ ወዳጆች ሆይ! ይህ ተስፋ ቃል ስላለን፥ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን እናንጻ፥ እግዚአብሔርን በመፍራት ቅድስናችንን ፍጹም እናድርግ።
እኛም በክርስቶስ ፍጹም አድርገን ሁሉንም ሰው ለማቅረብ ሁሉንም ሰው እየገሠጽንና ሁሉንም ሰው በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፤
ከእናንተ ወገን የሆነ የክርስቶስ ባርያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይተጋል።