La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 4:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነርሱም ወዲያውኑ ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወዲያውኑ ጀልባቸውንም ሆነ አባታቸውን ትተው ተከተሉት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱም ወዲያውኑ ጀልባዋንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 4:22
10 Referencias Cruzadas  

ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔም ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።


ከዚያም እልፍ ብሎ ሌሎች ሁለት ወንድማማቾች የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን በታንኳ ውስጥ ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር መረባቸውን ሲጠግኑ አየና ጠራቸው።


ኢየሱስም በምኵራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትን ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝቡ መካከል ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዘዋወር ነበር።


ወዲያውኑ ጠራቸው። እነርሱም ከቅጥር ሠራተኞቹ ጋር አባታቸውን በጀልባው ላይ ትተው ተከትለውት ሄዱ።


“ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት እንኳን ሳይቀር ካልናቀ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።


እንግዲህ እንደዚሁ ከእናንተ ያለውን ሁሉ የማይተው ማንም ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።


ታንኳዎቹንም ወደ ምድር አድርሰው ሁሉን ትተው ተከተሉት።


ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሰብአዊ አመለካከት እንደምናየው አድርገን አንመለክትም፤ ክርስቶስንም በዚህ መልክ ተመልክተነው የነበርን ብንሆን እንኳን፥ ከእንግዲህ ወዲህ ግን በዚህ መልክ አይደለም የምናውቀው።