ማቴዎስ 26:71 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሊወጣ ወደ በሩ ሲሄድ ሌላዪቱ አየችውና በዚያ ለነበሩት “ይህም ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበረ” አለቻቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከግቢው መውጫ ወደ ሆነው በር ሲያመራ ሌላዋ ሠራተኛ ተመልክታው፣ በዚያ ለነበሩት ሰዎች፣ “ይህ ሰው ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋራ ነበር” አለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሊወጣ ወደ በሩ ሲሄድ አንዲት ሌላ ገረድ አየችውና እዚያ ለነበሩት ሰዎች “ይህ ሰው ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር ነበር!” አለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ በሩም ሲወጣ ሌላይቱ አየችውና በዚያ ላሉት “ይህ ደግሞ ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበረ፤” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ በሩም ሲወጣ ሌላይቱ አየችውና በዚያ ላሉት፦ ይህ ደግሞ ከናዝሬቱ ከኢየሱስ ጋር ነበረ አለች። |