La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 23:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እናንተ ዕውሮች! የትኛው ይበልጣል? መባው ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እናንተ ዕውሮች፤ ከመባውና መባውን ከቀደሰው መሠዊያ የቱ ይበልጣል?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እናንተ ዕውሮች! ከመባውና መባውን ከሚቀድሰው መሠዊያ የቱ ይበልጣል?

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች! ማናቸው ይበልጣል? መባው ነውን? ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች፥ ማናቸው ይበልጣል? መባው ነውን? ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው?

Ver Capítulo



ማቴዎስ 23:19
6 Referencias Cruzadas  

ሰባት ቀን ለመሠዊያው ማስተስረያ ታደርጋለህ፥ ትቀድሰዋለህም፤ መሠዊያውም ፍጹም ቅዱስ ይሆናል፤ መሠዊያውን የሚነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።


ቀድሳቸው ፍጹም የተቀደሱ ይሆናሉ፤ የሚነካቸውም ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።


አንድ ሰው የተቀደሰ ሥጋ በልብሱ ዕጥፋት ቢይዝ፥ ዕጥፋቱ እንጀራ ወይም ወጥ፥ ወይም የወይን ጠጅ፥ ወይም ዘይት፥ ወይም ማናቸውንም መብል ቢነካ ያ የተነካው የተቀደሰ ይሆናልን? ካህናቱም፦ አይሆንም ብለው መለሱ።


እናንተ ዕውሮችና ሞኞች! የትኛው ይበልጣል? ወርቁ ወይስ ወርቁን የቀደሰው ቤተ መቅደስ?


ደግሞም ‘ማንም በመሠዊያው ቢምል ምንም አይደለም፤ ማንም በላዩ ላይ ባለው መባ ቢምል ግን በመሐላው ይያዛል፤’ ትላላችሁ።


ስለዚህ በመሠዊያው የሚምል በመሠዊያውና በእርሱ ላይ ባለው ሁሉ ይምላል፤