ማቴዎስ 21:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመጨረሻም ‘ልጄንስ ያከብሩታል’ ብሎ ልጁን ላከባቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመጨረሻም፣ ‘ልጄንስ ያከብሩታል’ በማለት ልጁን ላከ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጨረሻም የወይኑ አትክልት ጌታ ‘ልጄንስ ያከብሩታል!’ በማለት ልጁን ወደ ገበሬዎቹ ላከ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኋላ ግን ‘ልጄንስ ያፍሩታል፤’ ብሎ ልጁን ላከባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኋላ ግን፦ ልጄንስ ያፍሩታል ብሎ ልጁን ላከባቸው። |
ምናልባት የይሁዳ ቤት እኔ ላደርግባቸው ያሰብኩትን ክፉ ነገር ሁሉ ይሰሙ ይሆናል፥ ከዚህም የተነሣ ሁላቸውም ከክፉ መንገዳቸው ተመልሰው በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር እል ይሆናል።”
እኔም አልኩ “በእርግጥ ትፈሪኛለሽ፥ እርማትንም ትቀበያለሽ፤ መኖሪያዋ አይጠፋም፥ ያቀድኩትም አይደርስም።” እነርሱ ግን በማለዳ ተነሥተው ድርጊታቸውን ሁሉ አረከሱ።
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።