La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 18:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህን ልትምረው አይገባህም ነበርን?’

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔ እንደ ማርሁህ አንተም ባልንጀራህን ልትምረው አይገባህም ነበርን?’

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ታዲያ፥ እኔ ዕዳህን እንደ ተውኩልህ፥ አንተስ ባልንጀራህ ለሆነው አገልጋይ ዕዳውን ልትተውለት አይገባህም ነበርን?’

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን?’ አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን? አለው።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 18:33
9 Referencias Cruzadas  

ከዚያ በኋላ ጌታው ጠርቶ እንዲህ አለው፦ ‘አንተ ክፉ ባርያ፥ ስለ ለመንኸኝ ያን ሁሉ ዕዳ ተውሁልህ፤


ጌታውም ተቆጥቶ ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍል ድረስ ለሚያሠቃዩት አሳልፎ ሰጠው።


ምሕረት የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፤ ምሕረትን ያገኛሉና።


እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤


እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።


እርስ በርሳችሁ ተቻቻሉ፤ ማንም ሰው በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ ይቅር በሉ፤