La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 17:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ ቅፍርናሆም በደረሱ ጊዜ ሁለት ዲናር የሚቀበሉ ሰዎች ወደ ጴጥሮስ ቀረቡና “መምህራችሁ ሁለት ዲናር አይከፍልምን?” አሉት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ቅፍርናሆም ከደረሱ በኋላ፣ የቤተ መቅደሱ ግብር ተቀባዮች ወደ ጴጥሮስ ቀርበው “መምህራችሁ ሁለቱን ዲናር የቤተ መቅደስ ግብር አይከፍልምን?” አሉት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ቅፍርናሆም በደረሱ ጊዜ የቤተ መቅደስ ግብር ተቀባዮች ወደ ጴጥሮስ ቀረቡና፥ “መምህራችሁ የቤተ መቅደስ ግብር አይከፍልምን?” ሲሉ ጠየቁት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ቅፍርናሆምም በመጡ ጊዜ ግብር የሚቀበሉ ሰዎች ወደ ጴጥሮስ ቀረቡና “መምህራችሁ ሁለቱን ዲናር አይገብርምን?” አሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ቅፍርናሆምም በመጡ ጊዜ ግብር የሚቀበሉ ሰዎች ወደ ጴጥሮስ ቀረቡና፦ መምህራችሁ ሁለቱን ዲናር አይገብርምን? አሉት።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 17:24
5 Referencias Cruzadas  

የምድሪቱ ሕዝቦች ሸቀጥ ወይም ልዩ ልዩ እህል ለመሸጥ በሰንበት ቀን ቢያመጡ፥ በሰንበት ወይም በተቀደሰ ቀን ከእነርሱ አንገዛም፤ በሰባተኛው ዓመትም ምድሪቱን እናሳርፋታለን፥ ዕዳንም ሁሉ እንሰርዛለን።


በቆጠራው የሚያልፉ ሁሉ ይህን ይስጡ፥ በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት ግማሽ ሰቅል ይሰጣል፥ ሰቅል ሃያ ጌራ ነው፤ ግማሽ ሰቅል ለጌታ ስጦታ ነው።


በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት፥ የሰቅል ግማሽ ከተቆጠረው ከእያንዳንዱ ሰው የተሰጠ ነው፤ ይህም ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያ በላይ የተቆጠሩት ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ሰዎች ነበሩ።


የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ሽልማት ታገኛላችሁ? ቀራጮች እንኳ ይህንኑ ያደርጉ የለምን?


ከዚህ በኋላ ወደ ቅፍርናሆም መጡ። ቤት ከገባ በኋላም፥ “በመንገድ ላይ የምትከራከሩት ስለምን ነበር?” ብሎ ጠየቃቸው።