La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 12:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፈሪሳውያን ግን ወጥተው እንዴት አድርገው እንደሚያጠፉት ተማከሩ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ፈሪሳውያን ግን ከዚያ ወጣ ብለው ኢየሱስን እንዴት እንደሚገድሉት ተማከሩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ፈሪሳውያን ግን ከዚያ ወጥተው ኢየሱስን እንዴት አድርገው እንደሚገድሉት ተማከሩ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፈሪሳውያን ግን ወጥተው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ተማከሩበት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፈሪሳውያን ግን ወጥተው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ተማከሩበት።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 12:14
15 Referencias Cruzadas  

ኢየሱስን በተንኰል ይዘው ሊገድሉት ተማከሩ፤


በነጋም ጊዜ ሊቃነ ካህናትና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ሁሉ ኢየሱስን ሊገድሉት ተማከሩ፤


የፋሲካና የቂጣ በዓል ሊከበር ሁለት ቀን ሲቀረው፥ የካህናት አለቆችና ጸሐፍት ኢየሱስን የሚይዙበትና የሚገድሉበትን ዘዴ ይፈልጉ ነበር።


ፈሪሳውያንም ወጥተው ወዲያው እንዴት አድርገው እንደሚያጠፉት ከሄሮድስ ሰዎች ጋር ተማከሩበት።


የካህናት አለቆችና ጻፎች እርሱን የሚገድሉበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር፤ ሕዝቡን ይፈሩ ነበርና።


እነርሱ ግን በቁጣ ተሞሉ፤ በኢየሱስም ላይ ምን እንደሚያደርጉበት እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ።


አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ አነሡ።


ደግመኛም ሊይዙት ፈለጉ፤ ከእጃቸውም አምልጦ ሄደ።


እንግዲህ ከዚያ ቀን ጀምረው ሊገድሉት ተማከሩ።


የካህናት አለቆችም ፈሪሳውያንም ይይዙት ዘንድ እርሱ ያለበትን ስፍራ የሚያውቅ ሰው ቢኖር እንዲያመለክታቸው አዝዘው ነበር።


እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን ደግሞ እራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ “እግዚአብሔር አባቴ ነው፤” ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር።


ስለዚህ ሊይዙት ይፈልጉ ነበር፤ ነገር ግን ጊዜው ገና ስላልደረሰ ማንም እጁን አልጫነበትም።


ፈሪሳውያን ሕዝቡ ስለ እርሱ እንደዚህ ሲያንጐራጉሩ ሰሙ፤ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ሊይዙት ዘቦችን ላኩ።


ከእነርሱም አንዳንዶቹ ሊይዙት ፈለጉ፤ ነገር ግን እጁን ማንም አልጫነበትም።


ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወረባቸው፥ ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ።