ማርቆስ 8:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡም በልተው ጠገቡ፤ ከዚያም ደቀመዛሙርቱ የተረፈውን ቁርስራሽ ሰባት መሶብ ሙሉ አነሡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡም በልተው ጠገቡ፤ ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ የተረፈውን ቍርስራሽ ሰባት መሶብ ሙሉ አነሡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎቹም ሁሉ በልተው ጠገቡ፤ የተረፈውንም ቊርስራሽ ሰብስበው ሰባት ትላልቅ መሶብ ሙሉ አነሡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሉም፤ ጠገቡም፤ የተረፈውንም ቍርስራሽ ሰባት ቅርጫት አነሡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሉም ጠገቡም፥ የተረፈውንም ቍርስራሽ ሰባት ቅርጫት አነሡ። |
ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን የለዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው መብል ሥሩ፤ ይህም የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ነው፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”