ወዲያው እንደ ወረዱም፥ ሕዝቡ ኢየሱስን ዐወቁት፤
ወዲያው ከጀልባዋ እንደ ወረዱም፣ ሕዝቡ ኢየሱስን ዐወቁት፤
ከጀልባ እንደወረዱ ወዲያውኑ ሰዎች ኢየሱስን ዐወቁት፤
ከታንኳይቱም ሲወጡ ወዲያው አውቀውት
ጌታ ለተጨቆኑ መጠጊያ ይሁናቸው፥ በመከራም ጊዜ መሸሸጊያ ይሁንላቸው።
በተሻገሩም ጊዜ፥ ጌንሴሬጥ ደርሰው ወረዱ፤ ጀልባዋንም እዚያው አቆሙ።
ወደ አካባቢውም ሁሉ በመሮጥ ሕመምተኞችን በዐልጋ ላይ እየተሸከሙ እርሱ ወደሚገኝበት ስፍራ ሁሉ ያመጡ ነበር።
ይህም በሆነ ጊዜ የቀሩት ደግሞ በደሴቲቱ ደዌ የነበረባቸው እየመጡ ተፈወሱ፤
በሞቱም እርሱን በመምሰል ክርስቶስንና የትንሣኤውን ኃይል መከራውንም ተካፋይ መሆኔን ማወቅ እፈልጋለሁ፤