ማርቆስ 4:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውሃ በታንኳይቱ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በታንኳይቱ ይገባ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስ ተነሣ፤ ማዕበሉም ውሃ እስኪሞላት ድረስ ጀልባዋን ያናውጣት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብርቱ ዐውሎ ነፋስ ተነሥቶ ውሃው በጀልባው እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ ጀልባውን ይመታ ጀመር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውሃ በታንኳይቱ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በታንኳይቱ ይገባ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብርቱ ዐውሎ ነፋስም ተነሣና ውኃ በታንኳይቱ እስኪሞላ ድረስ ማዕበሉ በታንኳይቱ ይገባ ነበር። |
እነሆም፥ ብርቱ ነፋስ ከምድረበዳ መጥቶ የቤቱን አራቱን ማዕዘን መታው፥ በብላቴኖቹም ላይ ወደቀ፥ ሞቱም፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ።”
ነገር ግን ሁለት ባሕር በተገናኙበት ስፍራ ወድቀው መርከቡን በዲብ ላይ ነዱ፤ በስተ ፊቱም ተተክሎ የማይነቃነቅ ሆነ፤ በስተ ኋላው ግን ከማዕበሉ ግፊያ የተነሣ ይሰበር ነበር።