ማርቆስ 3:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙ ሰዎችን አድኖ ነበርና፥ በሕመም የሚሠቃዩ ሁሉ በእጃቸው ሊነኩት ፈልገው ያጨናንቁት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙዎችን ፈውሶ ስለ ነበር፣ በሕመም የሚሠቃዩ ሁሉ ሊዳስሱት ይሽቀዳደሙ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ ሰዎችን ከበሽታ ፈውሷቸው ነበርና በሕመም የሚሠቃዩ ሁሉ በእጃቸው ሊነኩት ፈልገው፥ ያጨናንቁት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙ ሰዎችን አድኖ ነበርና፥ ስለዚህም ሥቃይ ያለባቸው ሁሉ እንዲዳስሱት ይወድቁበት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብዙ ሰዎችን አድኖ ነበርና፥ ስለዚህም ሥቃይ ያለባቸው ሁሉ እንዲዳስሱት ይወድቁበት ነበር። |
ኢየሱስም በምኵራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትን ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝቡ መካከል ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዘዋወር ነበር።
በየደረሰበት መንደር ወይም ከተማ ወይም ገጠር ሁሉ ሕመምተኞችን በየአደባባዩ እያስቀመጡ የልብሱን ጫፍ እንኳን ለመንካት ይለምኑት ነበር፤ የነኩትም ሁሉ ይድኑ ነበር።
ከታንኳዎቹም የስምዖን ወደነበረችው ወደ አንዲቱ ገብቶ ከምድር ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጋት ጠየቀው፤ በታንኳይቱም ተቀምጦ ሕዝቡን ያስተምር ነበር።
ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር።