ማርቆስ 11:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም፥ “ምን ማድረጋችሁ ነው?” ቢላችሁ፥ “ለጌታ ያስፈልገዋል፤ በቶሎም መልሶ ይልከዋል” ብላችሁ ንገሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንም፣ ‘ምን ማድረጋችሁ ነው?’ ቢላችሁ፣ ‘ለጌታ ያስፈልገዋል፤ እርሱም ወዲያውኑ መልሶ ይልከዋል’ በሉት።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንም ሰው ‘ለምን ይህን ታደርጋላችሁ?’ ቢላችሁ፥ ‘ጌታ ስለሚያስፈልገው ነው፤ ወዲያውኑ መልሶ ይልከዋል፤’ በሉት።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማንም ‘ስለ ምን እንዲህ ታደርጋላችሁ?’ ቢላችሁ ‘ለጌታ ያስፈልገዋል፤’ በሉት፤ ወዲያውም ደግሞ ወደዚህ ይሰደዋል፤” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንም፦ ስለ ምን እንዲህ ታደርጋላችሁ? ቢላችሁ፦ ለጌታ ያስፈልገዋል በሉት፥ ወዲያውም ደግሞ ወደዚህ ይሰደዋል አላቸው። |
ሲጸልዩም “የሁሉን ልብ የምታውቅ አንተ ጌታ ሆይ! ይሁዳ ወደ ገዛ ራሱ ስፍራ ይሄድ ዘንድ በተዋት በዚህች አገልግሎትና ሐዋርያነት ስፍራን እንዲቀበል የመረጥኸውን ከእነዚህ ከሁለቱ አንዱን ሹመው፤” አሉ።
የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ ታውቃላችሁ፤ ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች እንድትሆኑ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ።