ማርቆስ 1:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከውሃው በሚወጣበትም ጊዜ፥ ሰማያት ተከፍተው፥ መንፈስ ቅዱስ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ሲወርድ አየ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከውሃው በሚወጣበትም ጊዜ፣ ሰማያት ተከፍተው፣ መንፈስ ቅዱስ እንደ ርግብ በርሱ ላይ ሲወርድ አየ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሐንስም ወዲያውኑ ኢየሱስ ከውሃው እንደ ወጣ ሰማይ ሲከፈትና መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ሆኖ በእርሱ ላይ ሲወርድ አየ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወዲያውም ከውሃው በወጣ ጊዜ ሰማያት ሲቀደዱ መንፈስም እንደ ርግብ ሲወርድበት አየና “የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወዲያውም ከውኃው በወጣ ጊዜ ሰማያት ሲቀደዱ መንፈስም እንደ ርግብ ሲወርድበት አየና፦ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ |
በሠላሳኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ ከወሩም በአምስተኛው ቀን፥ በኮቦር ወንዝ በምርኮኞች መካከል ነበርሁ፥ ሰማያት ተከፈቱ፥ እኔም የእግዚአብሔርን ራእይ አየሁ።
ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያውኑ ከውኃ ወጣ፤ እነሆ ሰማያት ተከፈቱ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድና በእርሱ ላይ ሲያርፍ አየ፤
መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ፤ “የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል፤” የሚል ድምፅም ከሰማይ መጣ።