ሚልክያስ 2:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእውነት ትምህርት በአፉ ውስጥ ነበረ፥ በከንፈሩም ውስጥ ስሕተት አልተገኘም፤ ከእኔ ጋር በሰላምና በቅንነት ሄደ፥ ብዙዎችንም ከኃጢአት መለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እውነተኛ ትምህርት በአፉ ነበር፤ ምንም ዐይነት የሐሰት ነገር በአንደበቱ አልተገኘም፤ ከእኔ ጋራ በሰላምና በቅንነት ተራመደ፤ ብዙዎችንም ከኀጢአት መለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ እውነትን ያስተምሩ ነበር፤ በአንደበታቸውም ስሕተት አልተገኘም፤ ከእኔ ጋር በሰላምና በቅንነት ተመላልሰዋል፤ በትምህርታቸው ብዙዎችን ከበደል መልሰዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእውነት ሕግ በአፉ ውስጥ ነበረች፥ በከንፈሩም ውስጥ በደል አልተገኘበትም፣ ከእኔም ጋር በሰላምና በቅንነት ሄደ፥ ብዙ ሰዎችንም ከኃጢአት መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእውነት ሕግ በአፉ ውስጥ ነበረች፥ በከንፈሩም ውስጥ በደል አልተገኘበትም፥ ከእኔም ጋር በሰላምና በቅንነት ሄደ፥ ብዙ ሰዎችንም ከኃጢአት መለሰ። |
ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ትተሃልና ለእኔ ካህን እንዳትሆን ትቼሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።
ደቀ መዛሙርታቸውን ከሄሮድስ ሰዎች ጋር ላኩበት፤ እነርሱም እንዱህ አሉት “መምህር ሆይ! እውነተኛ እንደሆንህ የእግዚአብሔርንም መንገድ በእውነት እንደምታስተምር እናውቃለን፤ ለማንምም አታደላም፤ የሰውን ፊት አታይምና፤
እነርሱም መጥተው እንዲህ አሉት፤ “መምህር ሆይ፤ አንተ ትክክለኛ ሰው መሆንህን እናውቃለን፤ የሰዎች ማንነት ስለማይገድህም አታዳላም፤ የእግዚአብሔርን መንገድ ብቻ በእውነት ታስተምራለህ፤ ለመሆኑ ለቄሣር ግብር መክፈል ይገባል ወይስ አይገባም?
እነርሱም እንዲህ ሲሉ ጠየቁት “መምህር ሆይ! እውነትን እንደምትናገርና እንደምታስተምር በሰው ፊትም እንደማታደላ እናውቃለን፤ ይልቁንም በእውነት የእግዚአብሔርን መንገድ ታስተምራለህ፤
ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፦ “ማሳህ በተባለው ቦታ ለፈተንኸው፥ በመሪባ ውኃም ለተከራከርኸው፥ ቱሚምህን ለሌዊ ስጠው፥ ኡሪምህም ለዚህ ቅዱስ ሰው ነው፤