La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሚልክያስ 2:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

መፋታትን እጠላለሁና፥ ይላል ጌታ የእስራኤል አምላክ፥ ልብሱንም በሁከት የሚሸፍንን ሰው እጠላለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፤ ስለዚህ እንዳታታልሉ በመንፈሳችሁ ራሳችሁን ጠብቁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ፍችን እጠላለሁ” ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፤ “ልብሱን በግፍ ድርጊት የሚሸፍነውንም ሰው እጠላለሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ስለዚህ በመንፈሳችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፤ ታማኝነታችሁም አይጓደል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“እኔ የባልና የሚስትን መፋታት እጠላለሁ፤ ልብስን በፍትሕ አልባነት መሸፈንንም እጠላለሁ ሰውነቱን በልብስ እንደሚሸፍን በግፍ ሥራ የሚሸፍንን ሰው እጠላለሁ፤ ስለዚህ እምነተቢስ ከመሆን ተጠንቀቁ።” ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

መፋታትን እጠላለሁ፥ ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፥ ልብሱንም በግፍ ሥራ የሚከድነውን ሰው እጠላለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ስለዚህ እንዳታታልሉ መንፈሳችሁን ጠብቁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

መፋታትን እጠላለሁ፥ ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፥ ልብሱንም በግፍ ሥራ የሚከድነውን ሰው እጠላለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ስለዚህ እንዳታታልሉ መንፈሳችሁን ጠብቁ።

Ver Capítulo



ሚልክያስ 2:16
13 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ትዕቢት የአንገት ሐብላቸው፥ ዓመጽ መጐናጸፊያቸው ሆነ።


ጥፋቱን የሚሰውር አይለማም፥ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።


ልጄ ሆይ፥ ስለምን ጋለሞታ ሴት ትወድዳለህ? የሌላይቱንስ ብብት ለምን ታቅፋለህ?


ሰው በእርሱ ላይ ተዘርግቶ ቢተኛ አልጋው አጭር ነው፤ ሰውም ሰውነቱን መሸፈን ቢወድድ መጎናጸፊያ ጠባብ ነው።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ እናታችሁን የፈታሁበት የፍቺዋ ጽሕፈት የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለየትኛው ነው? እነሆ፥ ስለ ኃጢአታችሁ ተሸጣችኋል፥ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈታለች።


ድሮቻቸውም ልብስ አይሆኑላቸውም፥ ራሳቸውንም በሠሩት መሸፈን አይችሉም፤ ሥራቸውም የበደል ሥራ ነው፥ የግፍም ሥራ በእጃቸው ነው።


“ሚስቱን ፈቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፤ ባልዋም የፈታትን የሚያገባ ያመነዝራል።


ላገቡት ግን የምሰጠው ትእዛዝ ይህ ነው፤ ይህም ትእዛዝ የጌታ ነው እንጂ የእኔ አይደለም፤ ያገባች ሴት ከባሏ አትለይ፤