እየተነጋገሩ እርምጃቸውን ቀጠሉ፤ ከዚያም በኋላ የእሳት ፈረሶች የሚስቡአቸው የእሳት ሠረገሎች ድንገት በመካከላቸው ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ።
ሉቃስ 9:51 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስ የሚያርግበት ወራት በቀረበ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ፊቱን አቀና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ወደ ሰማይ የሚያርግበት ጊዜ በመቃረቡ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ቈርጦ ተነሣ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ የሚያርግበት ቀን በተቃረበ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ቈርጦ ተነሣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመውጣቱ ወራትም በቀረበ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ፊቱን አቀና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚወጣበትም ወራት በቀረበ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ፊቱን አቀና፥ |
እየተነጋገሩ እርምጃቸውን ቀጠሉ፤ ከዚያም በኋላ የእሳት ፈረሶች የሚስቡአቸው የእሳት ሠረገሎች ድንገት በመካከላቸው ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ።
ዐሥራ ሁለቱንም ወደ እርሱ አቅርቦ እንዲህ አላቸው “እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ ስለ ሰው ልጅም በነቢያት የተጻፈው ሁሉ ይፈጸማል።
እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሳለ፥ ወደ ኢየሩሳሌም በመቃረቡ፥ የእግዚአብሔርም መንግሥት ፈጥኖ እንደሚገለጥ ይገምቱ ነበርና፥ ተጨማሪ ምሳሌ ነገራቸው።
ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን፥ የወደዳቸውን እስከ መጨረሻው ወደዳቸው።
ከዚህም በኋላ በዓለም አይደለሁም፤ እነርሱ ግን በዓለም ናቸው፤ እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ። ቅዱስ አባት ሆይ! እነዚህን የሰጠኸኝ እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው።
የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም፦ በሥጋ ተገለጠ፥ በመንፈስ ጸደቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ በአሕዛብ መካከል ተሰበከ፥ በመላው ዓለም ታመነ፥ በክብር ዐረገ፥ የሚል ነው።
የእምነታችንንም ራስና ፍጽምና የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፥ ውርደቱንም ንቆ፥ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል።