La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 6:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢየሱስም ለእነርሱ መልሶ እንዲህ አለ፦ “ዳዊት በተራበ ጊዜ አብረውት ከነበሩት ጋር ያደረገውን ነገር አላነበባችሁምን?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “ዳዊት በተራበ ጊዜ ከባልንጀሮቹ ጋራ ያደረገውን ከቶ አላነበባችሁምን?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እርሱና አብረውት የነበሩት ሰዎች በተራቡ ጊዜ ዳዊት ያደረገውን አላነበባችሁምን?

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እር​ሱና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትም በተ​ራቡ ጊዜ ዳዊት ያደ​ረ​ገ​ውን አላ​ነ​በ​ባ​ች​ሁ​ምን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢየሱስም ለእነርሱ መልሶ፦ ዳዊት በተራበ ጊዜ እርሱ አብረውት ከነበሩ ጋር ያደረገውን፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ ከካህናት ብቻ በቀር መብላቱ ያልተፈቀደውን የመሥዋዕትን እንጀራ ይዞ እንደ በላ፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት ደግሞ እንደ ሰጣቸው ይህን አላነበባችሁምን? አለ።

Ver Capítulo



ሉቃስ 6:3
10 Referencias Cruzadas  

እርሱም እንዲህ ሲል መለሰ “ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት እንዳደረጋቸው አላነበባችሁምን?


“እነዚህ የሚሉትን ትሰማለህን?” አሉት። ኢየሱስም “አዎን እሰማለሁ፤ ‘ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ’ የሚለውን ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው።


ኢየሱስ እንዲህ አላቸው “‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፤’ የሚለውን ከቶ በመጽሕፍት አላነበባችሁምን?


ስለ ትንሣኤ ሙታን ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ እንዲህ ተብሎ የተነገረውን አላነበባችሁምን?


አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ።


ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፥ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ፤ የሚለውን የመጽሐፍ ቃል አላነበባችሁምን፤


ስለ ሙታን ግን እንደሚነሡ እግዚአብሔር “እኔ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ፤” እንዳለው በሙሴ መጽሐፍ በቁጥቋጦው ዘንድ የተጻፈውን አላነበባችሁምን?