La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 24:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው “ሕያዉን ለምን በሙታን መካከል ትፈልጉታላችሁ? እርሱ እዚህ የለም፤ ይልቁንም ተነሥቶአል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሴቶቹም ከመፍራታቸው የተነሣ በምድር ተደፍተው ሳሉ፣ ሰዎቹ እንዲህ አሏቸው፤ “ሕያው የሆነውን እርሱን ለምን ከሙታን መካከል ትፈልጋላችሁ?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሴቶቹም እጅግ ፈርተው ወደ መሬት አቀርቅረው ሳሉ ሰዎቹ፦ “ስለምን ሕያውን ከሙታን መካከል ትፈልጋላችሁ? አሉአቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፈር​ተ​ውም ፊታ​ቸ​ውን ወደ ምድር አቀ​ረ​ቀሩ። እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “ሕያ​ዉን ከሙ​ታን ጋር ለምን ትሹ​ታ​ላ​ችሁ?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው፦ ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።

Ver Capítulo



ሉቃስ 24:5
15 Referencias Cruzadas  

እርሷም በንግግሩ በጣም ደንግጣ፥ “ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ይሆን?” ብላ አሰበች።


እነርሱም በዚህ ሲገረሙ፥ እነሆ፥ ሁለት ሰዎች የሚያንጸባርቅ ልብስ ለብሰው ወደ እነርሱ ቀረቡ፤


ገና በገሊላ እያለ የነገራችሁን አስታውሱ፥


እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሣው፤ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና።


በዚህ በኩል የሚሞቱ ሰዎች አሥራትን ይቀበላሉ፤ በዚያ በኩል የሚቀበለው ሕያው ሆኖ እንደሚኖር የተመሰከረለት እርሱ ነው።


ሕያውም እኔ ነኝ፤ ሞቼም ነበርሁ፤ እነሆም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ሕያው ነኝ፤ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።


“በሰምርኔስም ወዳለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፥ ሞቶ የነበረው፥ ሕያውም የሆነው፥ ፊተኛውና መጨረሻው እንዲህ ይላል፦