ሉቃስ 22:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰማይም የሚያበረታው መልአክ ታየው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልአክም ከሰማይ ተገልጦለት አበረታታው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ የሚያበረታታው መልአክ ከሰማይ መጥቶ ታየው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚያበረታታው የእግዚአብሔር መልአክም ከሰማይ ታየው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰማይም መጥቶ የሚያበረታ መልአክ ታየው። |
“‘መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል፤ እግርህም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል’ ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ ራስህን ወደ ታች ወርውር” አለው።
የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም፦ በሥጋ ተገለጠ፥ በመንፈስ ጸደቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ በአሕዛብ መካከል ተሰበከ፥ በመላው ዓለም ታመነ፥ በክብር ዐረገ፥ የሚል ነው።
ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው።