La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 12:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከሕዝቡም አንድ ሰው “መምህር ሆይ! ርስቱን ከእኔ ጋር እንዲካፈል ለወንድሜ ንገረው፤” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከሕዝቡም መካከል አንድ ሰው፣ “መምህር ሆይ፤ ወንድሜ ውርስ እንዲያካፍለኝ ንገረው” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከሕዝቡም መካከል አንድ ሰው ኢየሱስን፦ “መምህር ሆይ፥ አባታችን ያወረሰንን ርስት እንዲያካፍለኝ እባክህ ለወንድሜ ንገረው” አለው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከሕ​ዝ​ቡም አንዱ፥ “መም​ህር ሆይ፥ ርስ​ቴን እን​ዲ​ያ​ካ​ፍ​ለኝ ለወ​ን​ድሜ ንገ​ረው” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከሕዝቡም አንድ ሰው፦ መምህር ሆይ፥ ርስቱን ከእኔ ጋር እንዲካፈል ለወንድሜ ንገረው አለው።

Ver Capítulo



ሉቃስ 12:13
7 Referencias Cruzadas  

አቤቱ፥ ከሰዎች፥ እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፥ ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፥ ልጆቻቸው ተትረፍርፎላቸዋል የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ።


ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፥ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፥ ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም፤ በአፋቸው ብዙ ፍቅር ይገልጣሉ፥ ልባቸው ግን ያልተገባ ጥቅማቸውን ይከተላልና።


መንፈስ ቅዱስ በዚያች ሰዓት ልትናገሩ የሚገባችሁን ያስተምራችኋልና።”


እርሱም “አንተ ሰው! ለዳኝነትና ለማከፋፈል ማን ነው በላያችሁ የሾመኝ?” አለው።


መልካም ሰው በልቡ ከሚገኘው መልካም መዝገብ መልካሙን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም በልቡ ከሚገኘው ክፉ መዝገብ ክፉውን ያወጣል፤ በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፉ ይናገራልና።


አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ ሰዎች መካከል የማያቋርጥ ጭቅጭቅን ነው፤ እንደነዚህ ያሉት ሰዎች እግዚአብሔርን መምሰል ሀብት ማግኛ ዘዴ መስሎ ይታያቸዋል።