ዘሌዋውያን 5:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ማናቸውም ሰው ኃጢአት ቢሠራ፥ ጌታም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዱን ቢተላለፍ፥ ባያውቅም፥ ያ ሰው በደለኛ ነው፥ ኃጢአቱንም ይሸከማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ማንኛውም ሰው ኀጢአት ቢሠራ፣ እግዚአብሔር አታድርጉ ብሎ ከከለከላቸው ትእዛዞች ሳያውቅ አንዱን ተላልፎ ቢገኝ በደለኛ ነው፤ በኀጢአቱም ይጠየቅበታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው ባለማወቅ ከእግዚአብሔር ትእዛዞች አንዲቱን ቢተላለፍ በደለኛ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሰው ባለማወቅ ኀጢአት ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፍ፥ ቢታወቀው፥ ኀጢአት ስለሆነችበትም ንስሓ ቢገባ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማናቸውም ሰው ኃጢአት ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፍ፥ ባያውቅም፥ ያ ሰው በደለኛ ነው፥ ኃጢአቱንም ይሸከማል። |
“ማናቸውም ሰው ቢተላለፍ፥ ሳያውቅም ለጌታ በተቀደሰው በማናቸውም ነገር ኃጢአትን ቢሠራ፥ ለበደል መሥዋዕት ለጌታ ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ ያመጣል፤ ተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ በብር ሰቅል እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ለበደል መሥዋዕት ያቀርበዋል።
ነውር የሌለበትን አውራ በግ ከመንጋው እንደ ግምጋሜህ መጠን ለበደል መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያመጣል፤ ካህኑም ሳያውቅ ስለ ሠራው ስሕተት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።
ያላወቀ ግን መገረፍ የሚገባውንም ያደረገ ጥቂት ይገረፋል። ብዙም ከተሰጠው ሰው ሁሉ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል፤ ብዙ አደራም ከተሰጠው ከእርሱ አብዝተው ይሹበታል።