ዘሌዋውያን 25:52 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ጥቂቶች ዓመታት ቢቀሩ ከእርሱ ጋር በመሆን ያሰላል፤ እርሱ ማገልገል እንደሚገባው የዓመታት መጠን የመቤዠቱን ዋጋ ይመልስ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስከ ኢዮቤልዩ ድረስ የሚቀረው ጥቂት ዓመት ከሆነም፣ በቀረው ዓመት መጠን የሚዋጅበትን መልስ ይክፈል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ጥቂቶች ዓመቶች ቢቀሩ ከእርሱ ጋር ይቈጥራል፤ እንደ ዓመቶቹም መጠን የመቤዠቱን ዋጋ ይመልስ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ጥቂት ዓመታት ቢቀሩ እንደ ዓመቱ ይቍጠሩለት፤ እንደ ኣመታቱም መጠን የመቤዠቱን ዋጋ ይመልስ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ጥቂቶች ዓመታት ቢቀሩ ከእርሱ ጋር ይቈጥራል፤ እንደ ዓመታቱም መጠን የመቤዠቱን ዋጋ ይመልስ። |