ለማስመለስ ግን በቂ ገንዘብ ባያገኝ፥ ሽያጩ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ በገዛው ሰው እጅ ይሆናል፤ በኢዮቤልዩ ዓመት ነፃ ይወጣል፥ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለሳል።
ዘሌዋውያን 25:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ዓመትም እስከሚፈጸም ባለው ጊዜ ሁሉ ባይቤዠው፥ ቅጥር ባለው ከተማ ውስጥ ያለው ቤት ለገዛው ሰው ለልጅ ልጁ ለዘለዓለም ይጸናለታል፤ በኢዮቤልዩም ከእርሱ ነፃ አይወጣም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሉው ዓመት ከማለቁ በፊት መዋጀት ካልቻለ ግን፣ ቅጥር በተሠራለት ከተማ ውስጥ ያለው ቤት የገዢውና የልጅ ልጆቹ ንብረት ሆኖ ይቀራል፤ በኢዮቤልዩ አይመለስለትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በዓመቱ ውስጥ መልሶ መዋጀት ባይችል፥ መልሶ የመዋጀት መብቱን ያጣል፤ ቤቱም ለገዛው ሰው ወይም ለዘሮቹ ቀዋሚ ንብረት ሆኖ ይቀራል፤ በኢዮቤልዩ ዓመት እንኳ ለሻጩ አይመለስለትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንድ ዓመት እስኪጨረስ ባይቤዠው ቤቱ ለገዡ ይሆናል፤ ቅጥር ባለበት ከተማ ያለውን ያን ቤት ይመረምሩለታል፤ ለገዛው ሰው ለልጅ ልጁ ለዘለዓለም ይጸናለታል፤ በኢዮቤልዩ ዓመትም አይወስዱበትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንድ ዓመትም እስኪጨረስ ባይቤዠው፥ ቅጥር ባለበት ከተማ የሚሆን ቤት ለገዛው ለልጅ ልጁ ለዘላለም ይጸናለታል፤ በኢዮቤልዩም ከእርሱ አይወጣም። |
ለማስመለስ ግን በቂ ገንዘብ ባያገኝ፥ ሽያጩ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ በገዛው ሰው እጅ ይሆናል፤ በኢዮቤልዩ ዓመት ነፃ ይወጣል፥ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለሳል።
“ማናቸውም ሰው ቅጥር ባለው ከተማ ውስጥ ያለ መኖሪያ ቤትን ቢሸጥ፥ ከተሸጠ በኋላ አንድ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ ለመቤዠት ይችላል፤ ለአንድ ሙሉ ዓመት የመቤዠት መብት አለውና።