ጌታ ለአባቴ ለዳዊት ‘ከአንተ በኋላ የማነግሠው ልጅህ ለእኔ ቤተ መቅደስ ይሠራልኛል’ ሲል ተስፋ ሰጥቶት ነበር፤ ከዚህም የተነሣ ለጌታ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ለመሥራት እነሆ፥ አሁን ወስኛለሁ።
ዘሌዋውያን 25:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድሪቱም ፍሬዋን ትሰጣለች፥ እስክትጠግቡም ድረስ ትበላላችሁ፤ በእርሷም ላይ በደኅንነት ትቀመጣላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድሪቱ ፍሬዋን ትሰጣለች፤ እስክትጠግቡ ትበላላችሁ፤ በዚያም ያለ ሥጋት ትኖራላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድሪቱም ራስዋ በቂ ሰብል ስለምታስገኝ የምትበሉትን ሁሉ አግኝታችሁ በምቾትና በሰላም ትኖራላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድሪቱም ፍሬዋን ትሰጣለች፤ እስክትጠግቡም ድረስ ትበላላችሁ፤ በእርስዋም ውስጥ ተዘልላችሁ ትኖራላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድሪቱም ፍሬዋን ትሰጣለች፥ እስክትጠግቡም ድረስ ትበላላችሁ፤ በእርስዋም ውስጥ በጸጥታ ትኖራላችሁ። |
ጌታ ለአባቴ ለዳዊት ‘ከአንተ በኋላ የማነግሠው ልጅህ ለእኔ ቤተ መቅደስ ይሠራልኛል’ ሲል ተስፋ ሰጥቶት ነበር፤ ከዚህም የተነሣ ለጌታ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ለመሥራት እነሆ፥ አሁን ወስኛለሁ።
በምድርም ለተዘራው ዘርህ ዝናብ ይሰጣል፥ ከምድርም ፍሬ የሚወጣ እንጀራ ወፍራምና ብዙ ይሆናል። በዚያም ቀን ከብቶችህ በሰፊ መስክ ይሰማራሉ፤
ብዙ መብል ትበላላችሁ፥ ትጠግቡማላችሁ፥ ከእናንተም ጋር ተአምራትን የሠራውን የጌታ የአምላካችሁን ስም ታመሰግናላችሁ፥ ሕዝቤም ለዘለዓለም አያፍርም።
ለእናተም እህሉን ማበራየቱ የወይኑን ዘለላ እስከሚቆረጥበት ወቅት ድረስ ይደርሳል፥ የወይኑንም ዘለላ መቁረጥ እህል እስከ ሚዘራበት ወቅት ድረስ ይደርሳል፤ እስክትጠግቡም ድረስ እንጀራችሁን ትበላላችሁ፥ በምድራችሁም ላይ በደኅንነት ትቀመጣላችሁ።
በምድሪቱም ላይ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ማንም ሳያስፈራራችሁ ያለ ስጋት ትተኛላችሁ፤ ክፉዎችንም አራዊት ከምድሪቱ አስወግዳለሁ፥ ሰይፍም በምድራችሁ ላይ አያልፍም።
ይሁን እንጂ ዮርዳኖስን ስትሻገሩና ጌታ አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር ስትቀመጡ፥ ያለ ሥጋት እንድትኖሩ በዙሪያችሁ ካሉት ጠላቶቻችሁ ሁሉ ያሳርፋችኋል።