ዘሌዋውያን 19:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የምድራችሁንም መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ እስከ እርሻችሁ ድንበር ድረስ ፈጽማችሁ አትሰብስቡ፥ የመከሩንም ቃርሚያ አትልቀሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘የምድራችሁን መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ፣ በዕርሻችሁ ዳርና ዳር ያለውን አትጨዱ፤ ቃርሚያውንም አትልቀሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የምድራችሁን መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ በእርሻችሁ ድንበር ያለውን እህል አትጨዱ፤ ስታጭዱ የቀረውንም ቃርሚያ ለመሰብሰብ ወደ ኋላ አትመለሱ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የምድራችሁንም መከር በሰበሰባችሁ ጊዜ የእርሻችሁን አጨዳ አታጥሩ፤ ስታጭዱም የወደቀውን ቃርሚያ አትልቀሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምድራችሁንም መከር በሰበሰባችሁ ጊዜ የእርሻችሁን ድንበር ፈጽማችሁ አትጨዱ፥ የመከሩንም ቃርሚያ አትልቀሙ። |
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ እኔ ወደምሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ መከሩን ባጨዳችሁ ጊዜ፥ የእናንተን መከር በኵራት ነዶ ወደ ካህኑ አምጡ፤
“የምድራችሁንም መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ እስከ እርሻችሁ ድንበር ድረስ ፈጽማችሁ አትሰብስቡ። የመከሩንም ቃርሚያ አትልቀሙ፤ ለድሀውና ለእንግዳው ተዉት። እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።”
ሞአባዊቱም ሩት ናዖሚንን፦ “በፊቱ ሞገስ ወደማገኝበት ሰው ተከትዬ እህል ለመቃረም ወደ እርሻ ልሂድ” አለቻት። እርሷም፦ “ልጄ ሆይ፥ ሂጂ” አለቻት።
ቦዔዝም ሩትን፦ “ልጄ ሆይ፥ ትሰሚያለሽን? ቃርሚያ ለመቃረም ወደ ሌላ እርሻ አትሂጂ፥ ከዚህም አትላወሺ፥ ነገር ግን አገልጋዮቼን ተከትለሽ ቃርሚ።