ዘሌዋውያን 15:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው የሚነካውን የሸክላ ዕቃ ይሰብሩታል፤ የእንጨቱም ዕቃ ሁሉ በውኃ ይታጠባል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ሰው የነካው የሸክላ ዕቃ ይሰበር፤ ከዕንጨት የተሠራ ዕቃ ከሆነ በውሃ ይታጠብ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈሳሽ ያለበት ሰው የነካው ማንኛውም የሸክላ ዕቃ ቢኖር ይሰበር፤ ከእንጨት የተሠራ ዕቃ ሁሉ በውሃ ይታጠብ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው የሚነካውን የሸክላ ዕቃ ይስበሩት፤ የዕንጨቱንም ዕቃ ሁሉ በውኃ ይጠቡት፤ ንጹሕም ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው የሚነካውን የሸክላ ዕቃ ይስበሩት፤ የእንጨቱም ዕቃ ሁሉ በውኃ ይታጠብ። |
ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው እጁን በውኃ ሳይታጠብ ማንንም ሰው ቢነካ፥ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።
ከዘይት ጋር በምጣድ ላይ ይዘጋጃል፤ ደኅና ተደርጎ ከተለወሰ በኋላ ታመጣዋለህ፤ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን የተጋገረውን የእህል ቁርባን ቈራርሰህ ታቀርበዋለህ።
የምንኖርበት ምድራዊ ድንኳን የሆነው ሕይወት ቢፈርስ፥ በሰማይ ዘላለማዊ የሆነ በእጅ ያልተሠራ፥ በእግዚአብሔር የታነጸ መኖሪያ እንዳለን እናውቃለን።