“በስምንተኛውም ቀን ነውር የሌለባቸውን ሁለት ተባት ጠቦት፥ ነውር የሌለባትንም አንዲት የዓመት እንስት ጠቦት፥ ለእህሉም ቁርባን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ የሆነ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ዘይትም ያለበትን አንድ የሎግ መስፈሪያ ይወስዳል።
ዘሌዋውያን 14:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም የበደሉን መሥዋዕት ጠቦትና ዘይትም ያለበትን የሎግ መስፈሪያ ይወስዳል፤ ካህኑም ለመወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት ይወዘውዛቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑም ለበደል መሥዋዕት የሚሆነውን የበግ ጠቦትና አንድ ሎግ ዘይት ይቀበል፤ የሚወዘወዝ መሥዋዕት በማድረግም በእግዚአብሔር ፊት ይወዝውዛቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑም የበጉን ጠቦትና የወይራውን ዘይት ተቀብሎ በእግዚአብሔር ፊት የመወዝወዝ መሥዋዕት አድርጎ ያቀርበዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም የበደሉን መሥዋዕት የበግ ጠቦት የማሰሮውንም ዘይት ይወስዳል፤ በእግዚአብሔርም ፊት ለቍርባን ያቀርበዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም የበደሉን መሥዋዕት ጠቦት የሎግ መስፈሪያውንም ዘይት ይወስዳል፤ ካህኑም ለመወዝወዝ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይወዘውዛቸዋል። |
“በስምንተኛውም ቀን ነውር የሌለባቸውን ሁለት ተባት ጠቦት፥ ነውር የሌለባትንም አንዲት የዓመት እንስት ጠቦት፥ ለእህሉም ቁርባን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ የሆነ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ዘይትም ያለበትን አንድ የሎግ መስፈሪያ ይወስዳል።
ካህኑም አንዱን ተባት ጠቦት ይወስዳል፤ እርሱንም ስለ በደል መሥዋዕት ያቀርበዋል፥ ጎን ለጎንም ዘይቱ ያለበትን የሎግ መስፈሪያውን፤ እነርሱንም ስለ መወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት ይወዘውዛቸዋል።
ለመግዛትም አቅሙ የሚፈቅድለትን ያህል ሁለት ዋኖሶች ወይም የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ያደርገዋል።
“እርሱም ጠቦትን ለማቅረብ በቂ ገንዘብ ባይኖረው፥ ስለ ሠራው ኃጢአት ለበደል መሥዋዕት ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንደኛውን ለኃጢአት መሥዋዕት ሌላውን ደግሞ ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለጌታ ያመጣል።