ዘሌዋውያን 14:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ካህኑም አንዱን ተባት ጠቦት ይወስዳል፤ እርሱንም ስለ በደል መሥዋዕት ያቀርበዋል፥ ጎን ለጎንም ዘይቱ ያለበትን የሎግ መስፈሪያውን፤ እነርሱንም ስለ መወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት ይወዘውዛቸዋል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 “ካህኑም ከተባዕቱ ጠቦቶች በመውሰድ ከሎግ ዘይቱ ጋራ የበደል መሥዋዕት አድርጎ ያቅርብ፤ የሚወዘወዝ መሥዋዕት በማድረግም በእግዚአብሔር ፊት ይወዝውዛቸው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ከዚህም በኋላ ካህኑ ተባዕት ከሆኑት ከሁለቱ የበግ ጠቦቶች አንዱን የሊትር አንድ ሦስተኛ ከሆነው የወይራ ዘይት ጋር ወስዶ የበደል ስርየት መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል። ካህኑ ይህን በመወዝወዝ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጎ ያቀርበዋል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ካህኑም አንዱን ጠቦት ወስዶ ስለ በደል መሥዋዕት ያቀርባል፤ ያንም አንድ ማሰሮ ዘይት ስለ ልዩ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይለየዋል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ካህኑም አንዱን ጠቦት ወስዶ ስለ በደል መሥዋዕት ያቀርበዋል፥ ያንንም የሎግ መስፈሪያ ዘይት፤ ስለ መወዝወዝ ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይወዘውዘዋል። Ver Capítulo |