ሰቈቃወ 3:53 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕይወቴን በጉድጓድ አጠፉ፥ በላዬም ድንጋይ ጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕይወቴን በጕድጓድ ውስጥ ሊያጠፉ ሞከሩ፣ ድንጋይም በላዬ አደረጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከነሕይወቴ ጒድጓድ ውስጥ ወርውረው የጒድጓዱን አፍ በድንጋይ ዘጉብኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠላቶች ሕይወቴን በጕድጓድ አጠፉ፤ በላዬም ድንጋይ ገጠሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕይወቴን በጕድጓድ አጠፉ፥ በላዬም ድንጋይ ጣሉ። |
ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! እንድትሰማኝ አሁን እለምንሃለሁ፤ እባክህ፥ ልመናዬ ወደ አንተ ይድረስ፤ በዚያ እንዳልሞት ወደ ጸሐፊው ወደ ዮናታን ቤት አትመልሰኝ።”
ኤርምያስንም ወሰዱት፤ በእስር ቤቱም አደባባይ ወደነበረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መልክያ ጉድጓድ ውስጥ ኤርምያስን በገመድ አውርደው ጣሉት። በጉድጓድም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አልነበረበትም፤ ኤርምያስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።
“ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ነቢዩን ኤርምያስን በጉድጓድ ውስጥ ጥለው ባደረጉበት ነገር ሁሉ ክፉ ነገርን ፈጽመዋል፤ በከተማይቱም ውስጥ እንጀራ ስለ ሌለ በዚያ በራብ ይሞታል።”