መጽሐፈ ዮዲት 12:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባጎስም ከሆሎፎርኒስ ፊት ወጥቶ ወደ እርሷ ገባ፤ እንዲህም አላት፦ “ወደ ጌታዬ ለመምጣት፥ በፊቱም ለመከበር፥ ከእኛ ጋር ወይን ለመጠጣት፥ ዛሬ በናቡከደነፆር ቤት ከሚያገለግሉ የአሦር ልጆች አንዲቱ ለመሆን ይህች ቆንጆ አታመንታ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባግዋም ከሆሎፎርኒስ ዘንድ ወጥቶ ወደ እርሷ ገባ፥ “መልከ መልካም የሆንሽ አንቺ ልጄ ሆይ! ወደ ጌታዬ መምጣትን እንቢ አትበዪ፤ በእርሱ ዘንድ ትከብሪያለሽ፤ ከእርሱም ጋራ ወይንን ጠጥተሽ ደስ ይልሻል፤ በናቡከደነፆር ቤት ከሚያገለግሉት ከአሦር ልጆችም እንደ አንዲቱ ትሆኛለሽ” አላት። |